Home Back

በኦሮሚያ ክልል በርካታ ዞኖች በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች በወባ ተይዘዋል

voanews.com 2024/7/8
ፎቶ ፋይል፦ የወባ ትንኝ

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በርካታ ዞኖች፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን፣ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁት ዞኖች አንዱ በኾነው በምዕራብ ወለጋ ዞን ብቻ፣ ባለፉት ዐሥር ወራት ውስጥ፣ ከ500ሺሕ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን፣ የዞኑ የጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን ጣሰው ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

The code has been copied to your clipboard.

No media source currently available

በዚኹ ዞን የቆንዳላ ወረዳ ነዋሪዎች ደግሞ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ በወባ የሞቱ ሕፃናት መኖራቸውን ተናግረዋል። ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በመድኃኒት አቅርቦት ላይ እየሠራ መኾኑን፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ገልጿል።

People are also reading