Home Back

በኢትዮጵያ በግጭትና የተፈጥሮ አደጋ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

voanews.com 3 days ago
አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ፥ በግጭት፣ በድርቅ እና በሌሎችም ምክንያቶች፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሕፃናት፣ ክትባት አለመጀመራቸውንና ጀምረው ማቋረጣቸውንየጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ሚኒስቴር ደ’ኤታው ዶር. ደረጄ ዱጉማ፣ ትላንት ረቡዕ በሰጡት መግለጫ፣ ሕፃናቱን ተደራሽ ለማድረግ የዐሥር ቀናት የክትባት ዘመቻ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

የአፋር ክልል የጤና ቢሮም፣ ያልተከተቡ ሕፃናት ለተለያዩ የጤና እክሎች መዳረጋቸውን ጠቅሶ፣ በክትባት ዘመቻው 78ሺሕ ሕፃናትን ለማስከተብ ማቀዱን አመልክቷል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅትም በኢትዮጵያ የተጀመረውን የክትባት ዘመቻ እንደሚደግፍ ገልጿል፡፡

People are also reading