Home Back

የደቡብ አፍሪካው ኤኤንሲ በነጮች ከሚመራው ዲኤ ጋራ የአንድነት መንግስት መሰረተ

voanews.com 2024/7/3
በኬፕታውን የአዲሱ የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኤኤንሲ) መሪ ሲሪል ራማፎሳ ቃለ መሃላ ፈጸሙ ኬፕታውን እአአ ሰኔ 14/2024
በኬፕታውን የአዲሱ የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኤኤንሲ) መሪ ሲሪል ራማፎሳ ቃለ መሃላ ፈጸሙ ኬፕታውን እአአ ሰኔ 14/2024

ገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኤኤንሲ) የአፓርታይድ ስርዓት ካበቃበት ከዛሬ 30 ዓመታት ወዲህ ለዚያች ሃገር የመጀመሪያ የሆነውን ጥምር መንግስት ለመመስረት ከዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት ፓርቲ (ዲኤ) ጋራ በዛሬው ዕለት ከስምምነት ላይ ደርሷል።

ስምምነቱ የኤኤንሲው መሪ ሲሪል ራማፎሳ በፕሬዝዳንትነት ሥልጣናቸው እንዲቀጥሉ ቢያስችልም፤ የኢኤንሲ የ30 ዓመት የሥልጣን የበላይነት ማብቂያ ምልክት ሆኗል።

ባለፈው ግንቦት 21 በተካሄደው ምርጫ ከአጠቃላዩ የመራጭ ድምጽ 40 በመቶውን ብቻ በማግኘት በሃገሪቱ ፓርላማ የነበረውን አብላጫ ድምጽ ያጣ ሲሆን፤ የመሃል ቀኝ ዘመሙ የዲኤ ፓርቲ 21 በመቶውን ድምጽ አግኝቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ አናሳ ፓርቲዎች፣ የማህበራዊ ወግ አጥባቂው ኢንካታ የነፃነት ፓርቲ እና ቀኝ ዘመሙ የአርበኞች ህብረት የአዲሱ መንግስት አካል ይሆናሉ ተብሏል።

People are also reading