Home Back

በደቡብ አፍሪካ ፓርቲዎች የቅንጅት መንግሥት ለመመሥረት እየተነጋገሩ ነው

voanews.com 2024/7/3
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ምክትል ፕሬዛንት ፖውል ማሻቲሌ እና ግዌዴ ማንታሽ በተገኙበት ስለአዲስ መንግስ ምስረታ ውይይት ሲያደርጉ - ሰኔ 6፣ 2024
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ምክትል ፕሬዛንት ፖውል ማሻቲሌ እና ግዌዴ ማንታሽ በተገኙበት ስለአዲስ መንግስ ምስረታ ውይይት ሲያደርጉ - ሰኔ 6፣ 2024

በደቡብ አፍሪካ ከሣምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል አብላጫ ድምፅ ያገኘ ፓርቲ ባለመኖሩ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቅንጅት መንግሥት ለመመሥረት በመምከር ላይ ናቸው።

የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳም ሁሉም ወገኖች በመተባበር መንፈስ በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል።

ፓርቲያቸው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤ ኤን ሲ) ሃገሪቱ ከዘር መድልኦ አገዛዝ ከተላቀቀች ወዲህ ዝቅተኛ የሆነ ድምፅ አግኝቷል። በምርጫው ኤ ኤን ሲ 40 በመቶ ድምፅ በማግኘት ከፍተኛውን ውጤት ቢያስመዘግብም፣ መንግሥት ለመመሥረት ግን በቂ ድምፅ አልሆነም።

“ሃገሪቱ ለአዲስ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር በመዘጋጀት ላይ በመሆኗ፣ ሁሉም ፓርቲዎች ለተሃድሶና ለለውጥ በአንድነት መሥራት ይገባቸዋል” ብለዋል ራማፎሳ።

ኤ ኤን ሲ ሰፊ ልዩነት ካላቸው ቀኝም ሆነ ግራ ዘመም ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለመመሥረት ፈቃደኝነቱን ገልጿል።

አዲሱ ፓርላማ በሣምንት ውስጥ ሥራውን የሚጀምር ሲሆን፣ የመጀመሪያ ተግባሩም አዲስ መንግስት ለመመሥረት ፕሬዝደንቱን መምረጥ ይሆናል።

People are also reading