Home Back

ዴንማርክና ስሎቬኒያ አቻ ተለያዩ

fanabc.com 2024/7/8

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ዴንማርክ እና ስሎቬኒያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የዴንማርክን ጎል ክርስቲያን ኤሪክሰን በ17ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡

የስሎቬኒያን የአቻነት ጎል ጃንዛ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ቀደም ብሎ 10 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ከመመራት ተነስታ ፖላንድን 2 ለ1 አሸንፋለች፡፡

እንዲሁም ቀሪ የዛሬ የጨዋታ መርሐ-ግብር ሲቀጥል በምድብ ሦስት የሚገኙት ሰርቢያ እና እንግሊዝ ምሽት 4 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

People are also reading