Home Back

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች 3 ዋንጫዎችን በማንሣት የኢትዮጵያ ቦክስ ክለቦች ሻምፒዮን ሆነ

fanabc.com 2024/10/6

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በሦስት ዘርፎች የተካሄዱ ውድድሮችን በማሸነፍ የኢትዮጵያ ቦክስ ክለቦች ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡

በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን  አዘጋጅነት ለአራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የክለቦች የቦክስ ውድድር ተጠናቅቋል፡፡

በውድድሩ ሰባት ክለቦች የተካፈሉ  ሲሆን÷ የሴቶቹ ውድድር በ “ኤ” ምድብ እንዲሁም የወንዶቹ በ “ኤ” እና በ “ቢ” ተከፍሎ ጠንካራ ፉክክር በማስተናገድ ተካሂዷል፡፡

በውድደሩም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በ “ኤ” እና በ “ቢ” ምድቦች በማሸነፍ እንዲሁም ዓመቱን በከፍተኛ ነጥብ በማጠናቀቅ  ሦስት ዋንጫዎችን አንስቷል፡፡

እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በሴቶች የተካሄደውን ውድድር በማሸነፍ እና አጠቃላይ በሴቶች ከፍተኛ ነጥብ  በማስመዝገብ ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡

በሌላ በኩል ጸባይ ዋንጫ ተሸላሚ የሆነው የድሬዳዋ ከተማ ቦክስ ቡድን በሁለቱም ጾታ ኮከብ ቦክሰኛ ማስመረጥ መቻሉን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

People are also reading