Home Back

በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ከኦስትሪያ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

fanabc.com 2024/7/4

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚሁ መሠረት በምድብ አምስት የሚገኙት ሮማንያ እና ዩክሬን ቀን 10 ሠዓት እንዲሁም ቤልጂየም ከስሎቫኪያ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

በሌላ በኩል በምድብ አራት የሚገኙት ኦስትሪያ እና ፈረንሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል፡፡

ዛሬ በሚካሄዱ ጨዋታዎች ዩክሬን፣ ቤልጂየም እና ፈረንሳይ የማሸነፍ ዕድል እንዳላቸውም ቅድመ ጨዋታ ግምቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡

ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች እንግሊዝ ሰርቢያን 1 ለ 0 እንዲሁም ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ፖላንድን 2 ለ 1 ሲረቱ ስሎቬኒያ ከዴንማርክ አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡

People are also reading