Home Back

በአውሮፓ ዋንጫ ጀርመን ከስዊዘርላንድ እንዲሁም ስኮትላንድ ከሀንጋሪ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

fanabc.com 2024/10/5

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ጀርመን ከስዊዘርላንድ እንዲሁም ስኮትላንድ ከሀንጋሪ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

አዘጋጇ ሀገር ጀርመን ከሰዊዘርላንድ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በፍራንክፈርት አሬና ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን ያሸነፈው የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ያለመሸነፍ ክብሩን ለማስጠበቅ ወደ ሜዳ የሚገባ ሲሆን ሀንጋሪ በበኩሏ በምድቡ ሁለተኛ ደረጃን አስጠብቆ ለማለፍ ብርቱ ፉክክር እንደምታደርግ ይጠበቃል፡፡

በጨዋታው የጀርመኑ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ሁለት ጨዋታ ካሸነፈው ብሄራዊ ቡድናቸው መጠነኛ የአሰላልፍ ለውጥ እንደማያደርጉ ሲገለፅ፤ የስዊዘርላንዱ አሰልጣኝ ሙራት ያኪን በአንፃሩ የአሰላለፍ ለውጥ እንደማያደደርጉ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ ስኮትላንድ ከሀንጋሪ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በስቱትጋርቱ ኤም ኤች ፒ አሬና ስታዲየም ይደረጋል፡፡

በጨዋታው ስኮትላንድ ምርጥ ሶሰተኛ ሆና ለማለፍ  ያላትን ተስፋ ለመጠቀም ወደ ሜዳ የምትገባ ሲሆን በምድብ አንድ ግርጌ ላይ የምተገኘው ሀንጋሪም በተመሳሳይ በሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ ምርጥ ሶሰተኛ ሆና ለማለፍ ትጫዎታለች፡፡

People are also reading