Home Back

በ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አትሌት ሳሮን በርሄ አሸነፈች

fanabc.com 2024/10/5

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድርን በማሸነፍ አትሌት ሳሮን በርሄ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

በካሜሩን ዱዋላ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 5 የወርቅ ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች፡፡

እስከ አሁን በተካሄዱ ውድድሮችም ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የእርምጃ ውድድሮች 2 ወርቅ፣ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር 1 ወርቅ፣ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሠናክል 1 ብር እንዲሁም በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ነሐስ በማግኘት በአጠቃላይ አራት የወርቅ፣ 3 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች፡፡

People are also reading