Home Back

በምሥራቅ ጉራጌ ዞንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

voanews.com 2024/7/5
በምሥራቅ ጉራጌ ዞንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በምሥራቅ ጉራጌ ዞንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ አራት የማረቆ ብሔረሰብ አባላት በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

“ሟቾቹ ገበያ ውለው በተሽከርካሪ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ መንገደኞች ናቸው”፤ ያሉት ነዋሪዎቹ፣ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች ስድስት ሰዎችም በተለያዩ የሕክምና ተቋማት እየታከሙ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ንግሤ መኬ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ተፈፀመ በተባለው ጥቃት እስከ አሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ስድስት መድረሱን፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።

People are also reading