Home Back

በአውሮፓ ዋንጫ ቤልጂየም ከዩክሬን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

fanabc.com 2024/10/5

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ቤልጂየም እና ከዩክሬን ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ ምሽት አራት ወሳኝ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በዚህም ቤልጂየም ከዩክሬን እንዲሁም ፖርቹጋል ከጆርጂያ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው፡፡

በምድብ አምስት ምሽት 1 ሰዓት ላይ ቤልጂየም ከዩክሬን እንዲሁም ስሎቫኪያ ከሮማኒያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በዚህ ምድብ የሚገኙ ሁሉም ብሄራዊ ቡድኖች እኩል ሶስት ነጥብ በመያዝ ጥሎ ማለፉን የመቀላቀል እድል አላቸው፡፡

ስለሆነም ቡድኖቹ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀለል ከባድ ፉክክር እንደሚያደርጉ ነው የሚጠበቀው፡፡

በምድብ ስድስት ቱርክ እና ቼክ ሪፐብሊክን በማሸነፍ አስቀድማ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለችው ፖርቹጋል ምሽት 4 ሰዓት ላይ በምድቡ ግርጌ ከምትገኘው ጆርጂያ ጋር ትጫወታለች፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት በዚሁ ምድብ የምትገኘው ቱርክ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር የምትፋለም ይሆናል፡፡

ቱርክ አቻ መውጣት ብቻ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል የሚያስችላት ሲሆን÷ በአንጻሩ ቼክ ሪፐብሊክ ለማሸነፍ ትጫወታለች፡፡

People are also reading