Home Back

ለውጥ ለማምጣት የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ የጀመሩ የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች

voanews.com 2024/7/2
ለውጥ ለማምጣት የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ የጀመሩ የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች

በሀገራቸው ፓርላማ ያላቸው ውክልና አናሳ በመሆኑ እና ዛሬ ረቡዕ በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት መራጮች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ያበረታታቸው የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች በፖለቲካው ዘርፍ ለመሳተፍ ተነስተዋል።

የታወቀ የወጣቶች አንቂ የሆነው፣ ኢርፋን ማንጌራ የጋውቴንግ ክፍለ ሀገር የምክር ቤት መቀመጫ ለመያዝ ዕጩ ተፎካካሪ ሆኖ ቀርቧል።

"የቀደሙት ትውልዶች የፖለቲካ ውድቀት" ሲል በሚገልጸው የሐገሩ ችግር የተከፋው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሰሞኑን የመራጮችን ድጋፍ ለማግኘት ዘመቻ ሲያካሂድ ሰንብቷል።

ኢህሳን ሐፊጂ ከጆሐንስበርግ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

People are also reading