Home Back

ፖርቹጋል ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዋን ታደርጋለች

fanabc.com 2024/10/6

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ ምሽት ቱርክ ከፖርቹጋል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ 10 ሠዓት ላይ በምድብ 6 የሚገኙት ጆርጂያ እና ቼክ ሪፐብሊክ ይጫወታሉ፡፡

በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ጆርጂያ በቱርክ 3 ለ 1 እንዲሁም ቼክ ሪፐብሊክ በፖርቹጋል 2 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ያለምንም ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚሁ ምድብ የሚገኙት እና እኩል 3 ነጥብ ያላቸው ቱርክ እና ፖርቹጋል ምሽት 1 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ላይ በምድብ 5 የተደለደሉት ሮማንያ እና ቤልጂየም ይጫወታሉ፡፡

ሮማንያ ምድቡን በቀዳሚነት ስትመራ ቤልጂየም በአንጻሩ በምድቡ መጨረሻ ላይ ትገኛለች፡፡

በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 ስትረታ÷ ቤልጂየም በስሎቫኪያ 1 ለ 0 መሸነፏ ይታወሳል፡፡

People are also reading