Home Back

የአገራዊ ምክክር ሒደቱ የቀጠለበት ብሔራዊ ድባብ እንደሚያሳስባቸው ፓርቲዎች ገለጹ

voanews.com 2024/7/6
የአገራዊ ምክክር ሒደቱ የቀጠለበት ብሔራዊ ድባብ እንደሚያሳስባቸው ፓርቲዎች ገለጹ

አገር አቀፍ ውይይት የቀጠለበት ብሔራዊ ድባብ እንደሚያሳስባቸው የገለጹት፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/ኢሕአፓ/ እና እናት ፓርቲ በሀገራዊ በምክክር ሂደቱ ለመቀጠል ቅድመ ኹኔታዎችን አስቀመጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መላው ኢትዮጵያውያን በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበው፣ “ለሚያንገራግሩ ሰዎች ዕድሉ እንዳያመልጣችኹ” ብለዋል።

ይኹንና፣ በሒደቱ ላይ ጥያቄ እያነሡ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የኾነው ኢሕአፓ፥ ግጭቶች እንዲቆሙ፣ የፓርቲውን ሊቀ መንበር ጨምሮ የተለያዩ እስረኞች ካልተፈቱና ሌሎች ያነሣቸው ቅድመ ኹኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ራሱን ማግለሉን ዛሬ አስታውቋል።

እናት ፓርቲ በበኩሉ፣ ያስቀመጣቸው መሰል ቅድመ ኹኔታዎች ካልተሟሉ በምክክሩ ለመሳተፍ እቸገራለኹ፤ ብሏል፡፡

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሪፌሰር መስፍን አርኣያ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያነሧቸውን ጨምሮ ለሒደቱ መሳካት የሚያስፈልጉ ጥያቄዎችን፣ ኮሚሽኑ ለመንግሥት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።

People are also reading