Home Back

ትግራይ ክልል እየተጠቀመበት ባለው ዐዲስ ደንብ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ታዘዘ

voanews.com 2024/7/5
ትግራይ ክልል እየተጠቀመበት ባለው ዐዲስ ደንብ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ታዘዘ

የትግራይ ክልል፣ ካለፈው ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ እንዲኾን ያጸደቀው ደንብ ቁጥር 4/2016 እንዲሻር በቀረበው አቤቱታ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ መታዘዙን፣ ሂዩመን ራይትስ ፈርስት የተባለ፣ ሀገር በቀል የመብቶቸ ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ።

የድርጅቱ ምክትል ዲሬክተር አቶ መብርሂ ብርሃነ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሲናገሩ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የወጣው ደንብ፥ በጦርነቱ ወቅት ለወጡትና ከሕገ መንግሥቱ ጋራ ለሚቃረኑት ሕጎች እውቅና የሚሰጥ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ድርጅታቸው፣ ዐዲሱ ደንብ እንዲሻር፣ ለፌደራል የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ ማቅረቡን አመልክተዋል፡፡ጉባኤውም አቤቱታውን በመመልከት፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት ማዘዙን ተናግረዋል፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴርም በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ታዟል። ስለ ጉዳዩ ከትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

People are also reading