Home Back

የፈረንሳዩን ወግ አጥባቂ ቡድን ለመገዳደር ግራ እና መሃል ዘመሙ ቡድን ጥምረት ለመፍጠር እየጣሩ ነው

voanews.com 4 days ago
የቀኝ ዘመሙ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ እና መሪው ማሪን ለ ፔን
የቀኝ ዘመሙ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ እና መሪው ማሪን ለ ፔን

እሁድ እለት በፈረንሳይ የተካሄደውን የመጀመሪያ ዙሪ ምርጫ ያሸነፈው ቀኝ ዘመም ቡድን ስልጣን ለመቆጣጠር ተቃርቧል። አሸናፊውን ለመለየት ሰኔ 24 የሚካሄደውን ተጨማሪ ምርጫ ማሸነፍ ከቻሉም፣ በፓሪስ ከሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር በፊት መንግስት ሊቆጣጠር የሚያስችል እድል እንዳለው ተገልጿል።

በዚህ ስጋት የገባቸው ግራ እና መሃል ዘመም ፓርቲዎች ወግ አጥባቂዎቹን ለመገዳደር የሚያስችላቸው ጥምረት ለመፍጠር ጥሪ እያቀረቡ ነው።

ቀኝ ዘመሙ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ እና መሪው ማሪን ለ ፔን በውጤቱ ደስታቸውን እየገለፁ ሲሆን፣ ለ ፔን በፀረ-ስደት አቋሙ የሚታወቀውን ፓርቲያቸውን ከዘረኝነት እንቅስቃሴው ተቀባይነት ወዳለው የፖለቲካ አማራጭነት ለማሻሻል ለአመታት ሲጥሩ ቆይተዋል።

በእሁዱ ምርጫ አንድ ሦስተኛውን ድምፅ ካገኘው ብሔራው ንቅናቄ ተከትሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ግራ ዘመሙ ጥምረት ያገኘው ድምፅ 28 ከመቶ አይሞላም።

ወግ አጥባቂዎቹ በወንጀል እና በሕገወጥ ስደት ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው ሲሆን ቀጥሎ በሚካሄደው ምርጫ አብልጫ ድምፅ ካገኙ የብሔራዊ ንቅናቄው ፕሬዝዳንት ጆርዳን ባርዴላ ቀጣዩ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

People are also reading