Home Back

በሩዋንዳ በተካሄደ የቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

fanabc.com 2024/7/8

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደ የቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

በውድድሩ ገነት ፀጋዬ በ57 ኪሎ ግራም የሩዋንዳ ተጋጣሚዋን በብቃት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያና የውድድሩ ድንቅ እንስት ቡጢኛ በመባል የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች፡፡

በወንዶች ምድብ ደግሞ በ63 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ኢ/ር አብርሃም ዓለም የሩዋንዳ አቻውን በሰፊ ልዩነት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያውን አጥልቋል፡፡

በውደድሩ ኢትዮጵያ ምድቧን በበላይነት በማጠናቀቅ የዋንጫ ተሸላሚ ስትሆን÷ ብዙ ወርቅ በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃ መያዟንም የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

People are also reading