Home Back

በመቱ የሙሉ ወንጌል አማኞች ላይ ደረሰ የተባለው ድብደባ እንዲጣራ የአብያተ ክርስቲያናት ኅብረቱ ጠየቀ

voanews.com 2024/7/5
በመቱ የሙሉ ወንጌል አማኞች ላይ ደረሰ የተባለው ድብደባ እንዲጣራ የአብያተ ክርስቲያናት ኅብረቱ ጠየቀ

ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ በመቱ ከተማ ለወንጌል ስርጭት በወጡ የሙሉ ወንጌል አማኞች ላይ ደረሰ የተባለው ድብደባ እንዲጣራ፣ የኢሉ አባቦር አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ጠየቀ።

ተፈጽሟል በተባለው ድብደባ፣ ቢያንስ ዐሥር አማኞች ተጎድተው በሆስፒታል መታከማቸውን የገለጹት የኢሉ አባቦር አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ሰብሳቢ ቄስ ያደታ ደበላ፥ ድብደባውን ያደረሱ የጸጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲኾኑ፣ የመንግሥት ኃላፊዎችን እየጠየቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የመቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ተሻሌ ኤጀርሶ፣ ችግሩ ያጋጠመው፣ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ያለፈቃድ ለአደባባይ ስብከት መውጣታቸው መኾኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ፣ በዚያው በኢሉ አባቦር ዞን ዲዱ ወረዳ፣ ባለፈው ግንቦት 18 ቀን፣ በሰንበት የአምልኮ ሥርዐት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውን፣ የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

People are also reading