Home Back

አስተናጋጇ ጀርመን ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዋን ታደርጋለች

fanabc.com 2024/10/6

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት የመጀመሪያው ዙር የምድብ ማጠሪያ መጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ይጀመራል፡፡

በዚህም ባለፈው በስፔን 3 ለ 0 የተሸነፈችው ክሮሺያ በጣልያን 2 ለ 1 ከተረታችው አልባኒያ ጋር ቀን 10 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ላይ አስተናጋጇ ጀርመን ከሀንጋሪ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የመጀመሪያውን የምድብ ማጣሪያ ሀንጋሪ በስዊዘርላንድ 3 ለ 1 መሸነፏ ይታወሳል፡፡

በጀርመን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ልዩነት የተረታቸው ስኮትላንድም ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ስዊዘርላንድን ታስተናግዳለች፡፡

በምድብ አንድ ጀርመን ስዊዘርላንድን በማስከተል በምድቡ ቁንጮ የተቀመጠች ሲሆን÷ ምድብ ሁለትን ስፔን በቀዳሚነት ስትመራ ጣልያን ተከታዩን ደረጃ ይዛለች፡፡

People are also reading