Home Back

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል

fanabc.com 2024/7/8

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ወደ ውድድር ይመለሳል።

የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በሌላኛው የ27ኛ ሳምንት ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገም ቀጥሎ ሲካሄድ ፋሲል ከነማ ከመቻል ጋር ከቀኑ 9 ሰዓት እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ27ኛ እስከ 30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር መግለጹ ይታወቃል።

ሊጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ56 ነጥብ ሲመራ÷መቻል እና ባህር ዳር ከተማ ደግሞ በቅደም ተከተል በ51 እና በ45 ነጥብ ይከተላሉ፡፡

People are also reading