Home Back

የሙቀት መጨመር በጅቡቲ ተመላላሽ አሽከርካሪዎች ላይ ሞት እና የጤና ጉዳት አደረሰ

voanews.com 2024/7/5
የከባድ መኪና ተሽከርካሪዎች፣ ጂቡቱ
የከባድ መኪና ተሽከርካሪዎች፣ ጂቡቱ

ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባስከተለው ከፍተኛ ሙቀት የተነሣ፣ የጅቡቲ ተመላላሽ በኾኑ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ የሞት እና የጤና እክል ማጋጠሙን፣ የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር አስታወቀ።

ማኅበሩ እና አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች፣ የተቀናጀ የወረፋ ሥርዓት አለመኖሩ፣ አሽከርካሪዎች፣ ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ጅቡቲ ውስጥ ለረጅም ቀናት እንዲቆዩ እያደረጋቸው መኾኑ፣ ለአሽከርካሪዎቹ ኅልፈት እና ለጤና እክል ምክንያት እየኾነ እንዳለ ገልጸው ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡

The code has been copied to your clipboard.

No media source currently available

የነዳጅ አቅራቢ ባለንብረቶቸም ኾኑ ጉዳዩ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል፣ ዘመናዊ አሠራርን በመከተል በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እንዲቀንስ አስፈላጊውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማኅበር፣ ጅቡቲ ውስጥ አሽከርካሪዎች ተራቸውን በመጠበቅ የሚደርስባቸውን መጉላላት ለማስተካከል ውይይት ለማድረግ መታቀዱን አመልክቷል፡፡

People are also reading