Home Back

በዛሬ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኔዘርላንድስ ትጠበቃለች

fanabc.com 4 days ago

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምሽት አንድ ሠዓት ላይ ሮማንያ ከኔዘርላንድስ (ሆላንድ) በአሊያንዝ አሬና ስታዲያም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የዛሬው የጨዋታ መርሐ-ግብር ሲቀጥልም ምሽት አራት ሠዓት ላይ በሬድቡል አሬና ስታዲያም ኦስትሪያ ከቱርክ ይገናኛሉ፡፡

ምንም እንኳን የቅድመ ጨዋታ ግምቶች ኔዘርላንድስ እና ኦስትሪያ የማሸነፍ ዕድል እንዳላቸው ቢያመላክቱም ከተጋጣሚዎቻቸው ብርቱ ፈተና እንደሚጠበቅቻው ይገመታል፡፡

ቀደም ብለው በተካሄዱት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ፖላንድን 2 ለ 1 የረታችው ኔዘርላንድስ ከፈረንሳይ ጋር ያለምንም ጎል አቻ መለያየቷ እና በኦስትሪያ 3 ለ 2 መሸነፏ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም ኦስትሪያ በፈረንሳይ 1 ለ 0 ሽንፈት ማስተናገዷ እና ፖላንድን 3 ለ 1 እንዲሁም ኔዘርላንድስን 3 ለ 2 ማሸነፏ ይታወቃል፡፡

ትናንት በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ፈረንሳይ ቤልጂየምን 1 ለ 0 እንዲሁም ፖርቹጋል ስሎቬኒያን በመለያ ምት 3 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወቃል፡፡

People are also reading