Home Back

ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት በዳርፉር የጦር ወንጀል ተፈጽሟል መባሉን እየመረመረ ነው

voanews.com 2024/10/5
የዳርፉር ካርታ
የዳርፉር ካርታ

በሱዳን የዳርፉር መዲና በሆነችው አል ፋሺር የጦር ወንጀል እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ተፈጽሟል የሚሉ ክሶችን በመርመር ላይ መሆኑን ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት አስታውቋል።

አል ፋሺር በሱዳን ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ሰሞኑን ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደባት ይገኛል።

የችሎቱ ዋና አቃቤ ሕግ የሆኑት ካሪም ካን፣ የድምጽና የምስልን ጨምሮ ማንኛውም ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ለቢሯቸው እንዲልኩ ጠይቀዋል።

እስከ አሁን ለቢሯቸው የደረሱ ማስረጃዎች፤ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ጨምሮ በሲቪል ሕዝቦች ላይ ተደጋጋሚና እየቀጠሉ ያለ ጥቃቶች መፈፀማቸውን የሚከሱ እንደሆኑ ዋና አቃቤ ሕጉ አስታውቀዋል።

አስገድዶ መድፈርን ጭምሮ የተስፋፋ የጾታ ጥቃት መድረሱንም የተላኩት ማስረጃዎች እንደሚያሳዩ ጥቁመዋል። ሲቪሎች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ እየተደበደቡ መሆኑን፣ እንዲሁም በሆስፒታሎችም ሆኑ በሌሎች ተቋማት ላይ ዘረፋዎች መፈጸማቸውን ያሳያሉ ብለዋል።

አል ፋሺር 1.8 ሚሊዮን ነዋሪዎችና ተፈናቃዮች እንደሚገኙባት ሲታወቅ፣ 130 ሺሕ የሚሆኑት መኖሪያቸውን ጥለው ሸሽተዋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በከተማዋ በሚገኝ ብቸኛው ሆስፒታል ላይ ባለፈው እሁድ ጥቃት መፈጸሙን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አስታውቋል።

People are also reading