Home Back

በአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 አሸነፈች

fanabc.com 2024/10/5

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተካሄደ በሚገኘው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ቀደም ብሎ የአሸናፊነት ግምት ያልተሰጣት ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 ረትታለች፡፡

ኳስ ተቆጣጥሮ በመጫወት ብልጫ የነበራት ዩክሬን÷ ስታንቺዩ በ29ኛው፣ ማሪን በ53ኛው እና ድራጉስ በ57ኛው ደቂቃ ከመረብ ባሳረፏቸው ጎሎች ሽንፈት አስተናግዳለች፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ሮማንያ ሦስት ነጥብ በመያዝ በምድብ አምስት ቁንጮ ላይ ተቀምጣለች፡፡

17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ÷ በምድብ አምስት የሚገኙት ቤልጂየም እና ስሎቫኪያ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

እንዲሁም በምድብ አራት የሚገኙት ኦስትሪያ እና ፈረንሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል፡፡

ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች እንግሊዝ ሰርቢያን 1 ለ 0 እንዲሁም ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ፖላንድን 2 ለ 1 ሲረቱ ስሎቬኒያ ከዴንማርክ አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

People are also reading