Home Back

በአማራ ክልል በግጭት አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የእርሻ ሥራቸው መታጎሉን ገለጹ

voanews.com 2024/7/8
አርሶ አደሮች እርሻቸው ላይ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ፣አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ
አርሶ አደሮች እርሻቸው ላይ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ፣አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ

The code has been copied to your clipboard.

No media source currently available

በአማራ ክልል፣ በመንግሥት እና በፋኖ ቡድን ታጣቂዎች መካከል የቀጠለው ግጭት፣ በወቅቱ የእርሻ ሥራቸው ላይ ዕንቅፋት መፍጠሩን የተለያዩ አካባቢዎች አርሶ አደሮች አመልክተዋል፡፡

ግጭቶች የቀጠሉባቸው የምሥራቅ እና የምዕራብ ጎጃም ዞኖች ውስጥ ያሉ ቀበሌዎች አርሶ አደሮች፣ በቂ የአፈር ማዳበሪያም እያገኙ እንዳልኾነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምሳሉ ጎባው ደግሞ፣ ዘንድሮ ከ5ነጥብ8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ በወቅቱ መግባቱን ጠቅሰው፣ ከእዚኽም ውስጥ ከ4ነጥብ9 ሚሊየን በላይ ኩንታል ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል፤ ብለዋል፡፡

People are also reading