Home Back

የሩስያው ባህር ኃይል ምክትል ዋና አዛዥ ኤርትራ ናቸው

voanews.com 2024/5/17
በሩስያ ባህር ኃይል ምክትል ዋና አዛዥ፣ ምክትል አድሚራል ቭላድሚር ካሳቶኖቭ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ትናንት ከቀትር በኋላ ምጽዋ ገብቷል።
በሩስያ ባህር ኃይል ምክትል ዋና አዛዥ፣ ምክትል አድሚራል ቭላድሚር ካሳቶኖቭ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ትናንት ከቀትር በኋላ ምጽዋ ገብቷል።

የሩስያ ፌዴሬሽን እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱበትን 30ኛ ዓመት ለመዘከር የተሰናዱ ዝግጅቶች አካል መሆኑ በተነገረለት ሥነ ስርአት በሩስያ ባህር ኃይል ምክትል ዋና አዛዥ፣ ምክትል አድሚራል ቭላድሚር ካሳቶኖቭ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ትናንት ከቀትር በኋላ ምጽዋ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑን የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ፊሊጶስ ወልደዮሃንስ፣ የባህልና ስፖርት ኮሚሽነሩ አምባሳደር ዘመዴ ተክሌ እና ሌሎች ከፍተኛ የጦር አዛዦች መቀበላቸው ተዘግቧል።

ሩስያ በዩክሬን የፈጸመችውን ወረራ ተከትሎ ምዕራባውያን ሃገራት ከሞስኮ ጋራ በሚደረጉ የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ላይ ማዕቀቦችን ቢጥሉም፣ ኤርትራ በአንጻሩ ከሩስያ ጋራ ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው ከቀጠሉ ጥቂት አገራት አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

ኤርትራ በተጨማሪም የሩስያን ወረራ ያወገዘው የመንግሥታቱ ድርጅት፣ ባለፈው የካቲት ወር "ሞስኮ በአስቸኳይ ጦርነቱን እንድታበቃ እና ዩክሬንን ለቃ እንድትወጣ" ሲል አባል ሀገራት ድምጽ እንዲሰጡ ባደረገበት ወቅት ሩስያን ጨምሮ ውሳኔውን በመቃወም ድምጽ ከሰጡ ሰባት የድርጅቱ አባል ሀገራት ውስጥም አንዷ መሆኗ ይታወሳል።

People are also reading