Home Back

አሜሪካ ከኬንያ ጋራ ያላትን የጸጥታ ትብብር ከፍ አደረገች

voanews.com 2024/6/29
አሜሪካ ከኬንያ ጋራ ያላትን የጸጥታ ትብብር ከፍ አደረገች

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ዋሽንግተንን በመጎብኘት ላይ ላሉት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የተለመደውንና ሞቅ ደመቅ ያለውን አቀባበል አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ምሥራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር፣ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት አጋር እንድትኾን ወስነዋል። ኬንያ፣ ከሰሐራ በታች ካሉ ሀገራት ይህን ሚና ያገኘች የመጀመሪያዪቱ ሀገር ኾናለች፡፡

ውሳኔው፣ የአሜሪካ ወታደሮች፣ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኒዤር ለቀው ለመውጣት በሚዘጋጁበት ወቅት የመጣና አሜሪካ የጸጥታ ትብብሯን ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ማዞሯን የሚያመላክት ነው፤ ተብሏል።

የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል የላከችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

People are also reading