Home Back

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ሊሠሩ የሚችሉበትን ድንጋጌ የያዘ የዐዋጅ ረቂቅ ይፋ ኾነ

voanews.com 2024/7/5
የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ሊሠሩ የሚችሉበትን ድንጋጌ የያዘ የዐዋጅ ረቂቅ ይፋ ኾነ

የውጭ ባንኮች፣ በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ የሚሳተፉበትን አግባብ የሚዘረዝር “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” ተዘጋጅቶ ይፋ ኾኗል።

የዐዋጅ ረቂቁ፣ የውጭ ባንኮች፣ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት የሚይዙትን ተቀጥላ ወይም ቅርንጫፍ ለመክፈት ፈቃድ እንደሚያገኙ ይደነግጋል።

ይኸው ረቂቅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በዛሬ ኀሙስ ስብሰባው ላይ ውይይት ከሚያደርግባቸው የዐዋጆች ረቂቆች መካከል አንዱ እንደኾነ ተጠቅሶ የነበረ ቢኾንም ውይይት አልተደረገበትም።

መንግሥት፣ የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረጉ የተለያዩ ምክያቶች መኖራቸውን የሚያስረዱት የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ተንታኝ አቶ አማንይሁን ረዳ፣ በዘርፉ የውጭ ባንኮች ተሳትፎ አስፈላጊ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ ኾኖም፣ የውጭ ባንኮች ከሀገር ውስጥ ባንኮች ጋራ ተቀናጅተው ካልሠሩ አሉታዊ ተጽእኖዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

People are also reading