Home Back

በደቡብ አፍሪካ በሥልጣን ክፍፍል ሽኩቻ ካቢኔ መቋቋሙ ዘግይቷል

voanews.com 5 days ago
የደቡብ አፍሪካው ራማፎሳ ለሁለተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ ሲፈጸሙ እአአ ሰኔ 19/2024
የደቡብ አፍሪካው ራማፎሳ ለሁለተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ ሲፈጸሙ እአአ ሰኔ 19/2024

በደቡብ አፍሪካ የተዳከመው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) እና መንግስት ለመመሥረት የተቀናጀው ፓርቲ በካቢኔ የሥልጣን ክፍፍል ላይ ለመስማማት ባለመቻላቸው ምርጫው ከተካሄደ ከወር በኋላም ካቢኔ ሳይቁቋም ቀርቷል።

በድጋሚ በፕሬዝደንትነት የተመረጡት የ71 ዓመቱ ሰሪል ራማፎሳ የሃገሪቱ ፓርላማ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሐምሌ 18 ቀን እንዲከፈት ጥሪ አድርገዋል። ፓርቲያቸው ኤኤንሲ ምርጫውን በከፍተኛ ብልጫ ሳያሸንፍ በመቅረቱ፣ የብሔራዊ አንድነት መንግስት ብሎ የሚጠራውን የቅንጅት መንግስት ለመመስረት በመስራት ላይ ነው።

ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ከሆነውና 87 የፓርላማ መቀመጫዎችን ካሸንፈው “ዲሞክራቲክ አላያንስ” ጋራ የሚደረገው የስልጣን ድርድር ውጥረት የሚታይበት መሆኑን የሃገር ውስጥ ብዙሃን መገናኛዎች በመዘገብ ላይ ናቸው ሲል ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል። ኤኤንሲ በምርጫው 159 መቀመጫዎችን አግኝቷል።

“ዲሞክራቲክ አላያንስ” የካቢኔ ሥልጣን ከልክ በላይ ጠይቋል ሲል ኤኤንሲ በመክሰስ ላይ መሆኑን ሾልከው በመውጣት ለመገናኛ ብዙሃን እንዲደርሱ የተደረጉ ሰነዶች ማመልከታቸው ታውቋል።

People are also reading