Home Back

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ወደ ሥፍራው ሊያቀኑ ነው

voanews.com 2024/7/16
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሃመር
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሃመር

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሃመር ወደ ኢትዮጵያና ጅቡቲ ሊጓዙ እንደሆነ የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ዓርብ አስታውቋል።

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ጉዞው መቼ እንደሚካሄድ ባያስታውቅም፣ አምባሳደር ማይክ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ፣ በኢትዮጵያ መንግስትና በትግራይ ኃይሎች መካከል ፕሪቶሪያ ላይ የተፈረመውን የሠላም ስምምነት ተግባራዊነትን በሚገመግመው የአፍሪካ ኅብረት ሁለተኛ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል።

የውጪ ጉዳይ መ/ቤቱ ድህረ ገጽ በተጨማሪም፣ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስትንና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድርን ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆነች አመልክቷል። ይህም የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ በመበተን እና መልሶ በማቋቋም ላይ ያተኮረውን ፕሮግራም በመደገፍ፤ ተፈናቃዮችን በሠላም ወደ ቀያቸው በመመለስ፣ እንዲሁም የሽግግር ፍትህንና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃል።

አምባሳደር ማይክ ሃመር በተጨማሪም፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚታየውን ግጭት ለመፍታት ለውይይት ቅድሚያ በመስጥት ረገድ የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት በማድረግ ላይ ስላሉት ጥረት ይነጋገራሉ ተብሏል።

ልዩ ልዑኩ በጅቡቲ ቆይታቸው ቀጠናዊና የፀጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሃገሪቱ ባለሥልጣናት እንዲሁም ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ጋራ እንደሚወያዩ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

People are also reading