Home Back

የደቡብ አፍሪካ የአንድነት መንግሥት ካቢኔ ቃለ መሃላ ፈጸመ

voanews.com 3 days ago
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ

በደቡብ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው የአንድነት መንግሥት ካቢኔ ዛሬ ረቡዕ ቃለ መሃላ ፈጽሟል።

ከሠላሳ ዓመታት የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ገዢ ፓርቲነት ማክተም በኋላ፣ ከስድስት ፓርቲዎች የተውጣጡ 32 ሚኒስትሮች ያሉበት ካቢኔ ለመጀመሪያ ተቋቁሟል።

የ71 ዓመቱ ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ባለፈው እሁድ የአንድነት መንግስት መቋቋሙን አብስረዋል። የሚኒስትሮች ቁጥር ከ30 ወደ 32 ያደገ ሲሆን፣ 43 ምክትል ሚኒስትሮችም ይገኙበታል።

ደቡብ አፍሪካ ከነጮች የአፓርታይድ አገዛዝ ነፃ ከወጣችበት ከእ.አ.አ 1994 ወዲህ ሃገሪቱን ሲመራ የቆየው ኤ ኤን ሲ ባለፈው ግንቦት በተካሄደው ምርጫ በፓርላማው የበላይነት ባለማግኘቱ፣ የብሄራዊ አንድነት መንግሥት ለማቋቋም ተገዷል።

ፓርቲው የውጪ ጉዳይ፣ የገንዘብ፣ የመከላከያ፣ የፍትህ እና የፖሊስን ጨምሮ 20 የካቢኔ ሥልጣኖችን ይዟል።

ዋናው ተፎካካሪ የሆነው ዲሞክራቲክ አላያንስ 6 የሚኒስትር ቦታዎችን መያዙ ታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ትላንት ማክሰኞ ለራማፎሳ ስልክ በመደወል በምርጫው ድል በመቀዳጀታቸውና የብሔራዊ አንድነት መንግስት በተሳካ ሁኔታ በመመስረታቸው እንኳን ደስ አለህ እንዳሏቸው የራማፎሳ ቢሮ አስታውቋል።

People are also reading