Home Back

ፖርቹጋል የምትጠበቅበት የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል

fanabc.com 2024/10/5

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ፖርቹጋል ከቼክ ሪፐብሊክ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ፡፡

በዚህም በምድብ ሥድስት የሚገኙት ቱርክ እና ጆርጂያ ምሽት 1 ሠዓት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን÷ ጨዋታውን የማሸነፍ ዕድሉ ለቱርክ ተሰጥቷል፡፡

እንዲሁም በቅድመ ጨዋታ ግምት እንደምታሸንፍ የተገመተችው ፖርቹጋል ምሽት 4 ሠዓት ላይ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር የምታደርገው ፍልሚያ ትኩረት ስቧል፡፡

ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች ፈረንሳይ ኦስትሪያን እንዲሁም ስሎቫኪያ ቤልጂየምን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ሲያሸንፉ÷ ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 መርታቷ ይታወሳል፡፡

People are also reading